የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጥሏል፡፡

ቢሮው በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደስራ መገባቱ አስታውሷል።

በአሁኑ ወቅት ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ የዲያስፖራ አባላት ወደሀገራቸው እየገቡ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ወቅቱ የበዓል ሰሞን እንደመሆኑ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ በብዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ እና የዝርፊያ ምልክቶች እየታዩ ነው ሲል አሳውቋል።

ስለሆነ ከታህሳስ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.