የዲጂታል መታወቂያ ህትመትና ስርጭት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እንደገለጸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በማህተም ለሁሉም ክፍል ከተማ ሲያሰራጭ የነበረውን አሰራር ቀይሮ ህትመቱ በከተማ ባሉ በሁሉም ክፍለከተሞች ደረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቱ አንድ ነዋሪ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ብቻ እንዲኖረዉ ማድረግ እንደሚያስችል አስታውቋል::

ይህ ስርዓት ለነዋሪዎች የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ላይ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንም ኤጀንሲው አስታውቋል::

ኤጀንሲው አገልግሎቱን ወደ ስራ ከማስገባቱ አስቀድሞ ለሁሉም ክፍለ ከተማ የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች ስልጠናን መስጠቱንም አስታውቋል::

ህትመትና ስርጭት ወደ ክ/ከተማ መውረዱ ተገልጋዩ ህብረተሰብ የመታወቂያ ህትመት ለመውሰድ የሚፈጅበትን ጊዜ እና ገንዘብ እንደሚያስቀርም ተጠቁሟል::

አብድልሰላም አንሳር
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.