ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኬንያ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ቻይና የምትሾመው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በቀጠናው ያሉ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን የፀጥታ እና ደህንነት ስጋቶችን ለመቀልበስ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያሉ ሀገራ በሀገራቸው ውስጥ ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው ሊፈቱ ይገባል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በቀጠናው ሰላማዊ ድርድሮች እንዲካሄዱም ቻይና ሁኔታዎችን የሚያመቻች ተጠሪነቱ ለሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነ ልዩ መልዕክተኛ በቅርቡ ተልካለች ብለዋል።

ከኬንያ አቻቸው ጋር በወደብ ከተማዋ ሞምባሳ የተወያዩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ፤ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የቀጣናውን እጣ ፈንታ በእጃቸው ማስገባት አለባቸው ብለዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ ጉባኤ እንዲያደርጉም የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ሃሳብ አቅርበናል።

አሜሪካ ከ9 ወር በፊት የምስራቅ አፍሪካ ጉዳይን በቅርበት ለመከታተል በሚል ጄፍሪ ፌልትማንን የቀጠናው ልዩ መልእክተኛ አድርጋ መሾሟ ይታወሳል።

የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አሜሪካ በቀጠናው ካላት ልዩ መልእክተኛ ጋር አቻ ሚና እንደሚኖረው ዘገባው አመልክተቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *