በአሜሪካ የሜሪላንድ ሜዲካል ኮሌጅ፤ ከአሳማ ልብን በውሰድ የሰው ልብን መተካት ያስቻለ የተሳካ ሙከራ ማድጋቸው ተሰምቷል፡፡

የአሳማ ልብ ንቅለ ተከላው የተደረገለት ዴቪድ ቤኔት ለተባለው የ57 አመት እድሜ ላለው በልብ ሕመም ሲሰቃይ በነበረና ልቡ እንዳቆመች በሃኪሞች ለተነገረው ግለሰብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ዶክተሮች የመጨረሻ አማራጭ ይሆናል ያሉትን፤ ስራዋን ያቆመችው ልቡን በማስወገድ በአሳማ ልብ እንዲተካለት ሲሉ ይነግሩታል፡፡

ግለሰቡም ህይወቴ እንደሚያልፍ አውቅ ነበር፤ ቢሆንም ያለኝ አማራጭ ይሄው ከሓኪሞች የተነገረኝን ነገር መሞከረ ብቻ ነበር፣ እናም ፈቀደኛ ሆንኩ ይላል፡፡

የልብ ንቅለ ተከላውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 7 ሰዓታትን እንደወሰደ የሚለገጹት ዶክተሮቹ፤ ንቅለ ተከላው ከተደረገ ከ3 ቀናት በኋላ፤ አሁን ግለሰቡ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

ነገር ግን ይሄው ግለሰብ በአሳማ ልብ ለምን ያክል ጊዜ በጤንነት ሊቆይ አንደሚችል ግን የገለጹት ነገር የለም፡፡ ቢሆንም ግን በአለም የመጀመሪያው ከእንስሳት ወደ ሰው የተደረገ የተሳካ የልብ ንቅለ ተከላ እንደሆነ ነው ያመላከቱት፡፡

የግለሰቡን ንቅለ ተከላ ካደረጉት መካከል ሰርጂን ባርትለይ ግሪፊዝ እንዳሉት፤ ይህን ውሳኔ ለመወሰን ከዚህ በፊት፤ የእንሳሰት ልብ ወደ ሰዎች ከመግባታቸው በፊት አስፈላጊ የሆኑ ባዮሎጂካል ጥናቶች መደረጋቸውን ግልጸዋል፡፡

የአሁኑ ሙከራ በዚሁ በሽታ ምክንያት ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ለመታደግ አዲስ ተስፋ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጅበሪል መሐመድ

ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *