ሸገር ባስ በ6 ወር ውስጥ 59 ሚሊዮን ለሚጠጉ ደንበኞች አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ።

በግማሽ በጀት አመቱ በቀን በአማካይ 519 አውቶቢሶችን በማሰማራት እንዲሁም በአማካይ 425ሽህ ደንበኞችን በቀን በማገልገል 196.2 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ሸገር አስታውቋል።

ሸገር በስድስት ወራት ውስጥ 58.7 ሚሊዮን ህዝብ በማጓጓዝ 5.2 ሚሊዮን ኪሎ ሜትሮችን በመሸፈን 196.2 ሚሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ ውጤታማ ስራ መስራቱን የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እና የቴክኒክ ዘርፍ ሃላፊ ኢ/ር አዳነ አብደታ ተናግረዋል፡፡

ኢ/ር አዳነ አያይዘውም ሸገር በአሁኑ ሰዓት ተደራሽነቱን በማስፋት ከ120 በላይ የስምሪት መስመሮችን በማካለል በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.