የተጋነነ ታሪፍ አስከፍለው የተገኙ 14 የሀገር አቋራጭ አውቶቢሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ታታ አውቶቢሶች ከመናኸርያ ውጪ ወደ ጎንደር ከ1ሺህ ብር በላይ ታሪፍ እያስከፈሉ በመገኝታቸው ነው ተብሏል፡፡

በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር የትራንስፖርት ቁጥጥር ዳሬክተር አቶ ተስፋዬ አማረ ከኢትዮ ኤፍ ኤም እና ከተገልጋዩ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ባደረግነው ክትትል 14 የሀገር አቋራጭ ታታ ባሶች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት ስራ ላይ ያለው የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ታሪፍ 350 እንደሆነ የተናገሩት የልዩ አውቶቢሶች የታሪፍ መጠን 800 ብር እንደሆነ ነግረውናል፡፡

ከጥምቀት በአል አከባበር ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት የትራንስፖርት እጥረት እንደሌለ የተናገሩት አቶ ታምራት በሁሉም መናኸርያዎች በቂ የትራንስፖርት አቅርቦት አለ ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ ወደ ጎንደር ለማቅናት ዜጎች ለልዩ ባሶች እስከ 1500 ድረስ እየከፈሉ እንደነበረ ነው ለጣበያችን የገለጹት፡፡

እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተከራይተው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ባሶች እስከ ጥር 12 ቀን 2014 አመት ድረስ ትኬት ጨርሰናል የሚሉት በደላሎቻቸው አማካኝነት ተጨማሪ ገንዘብ ለማስከፍል በማሰባቸው ነው ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ዜጎች ከመናኸርያ ውጪ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ አውቶቢሶች እንዳይጠቀም ሚንስትር መስሪያ ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *