የከተማ ቤቶች መረጃ አስተዳደር ስርዓት ሶፍትዌር ትግበራ በይፋ መጀመሩ ተገለጸ

የከተሞችን የቤቶች መረጃ በአግባቡ ለማደራጀት፣ የቤት ፍላጎትና አቅርቦት ክፍተትን ለማጣጣም የሚያስችል የከተማ ቤቶች መረጃ አስተዳደር ስርዓት ሶፍትዌር ትግበራ በይፋ መጀመሩን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ ቤቶች መረጃ አስተዳደር ስርዓት የቤቶችን የመረጃ አያያዝ ከሌብነትና ከብልሹ አሰራሮች ለማላቀቅ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የከተማ ቤቶች መረጃ አስተዳደር ከመኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚታዩትን ብልሹ አሰራሮች በማቃለልና በማስተካካል በኩል ሶፍት ዌሩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው በከተማዋ የሚገኙ ክፍለ ከተማ አመራሮችም በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዲተገብሩት አሳስበዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርም የህዝብን ችግር ለመፍታት ቁልፍ ሚና ያለውን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ያልተደራጀ የቤቶች መረጃ አያያዝ ከፍተቶችንና ይቀርፋል ሲሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡

የህዝብን ችግር ለመፍታት ቁልፍ ሚና ያለውን ሶፍትዌሩ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርም ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *