ዛሬ ከቀትር 8 ሰዓት ገደማ ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኙት የግንባታ ዕቃዎች መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።

የእሳት አደጋው በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስትያን እና በአትላስ እንዲሁም በፀጋ ሆስፒታል መሃል ላይ በሚገኙት የንግድ ሱቆች መጋዘኖች ላይ በግምት 7፡40 አካባቢ መነሳቱን በስፍራው ተገኝተን ለማየት ችለናል።

የአደጋው መነሻ እስካሁን ያልተገለፀ ቢሆንም፤ እሳቱ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶ እንደነበር ባደረባችን በቦታ ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡
የተነሳው እሳት አደጋ ከ 7፡40 ጀምሮ እስከ 9፡20 ድረስ ሲነድ እንደነበር ና የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደርጉት የነበረው ርብርብ የሚደነቅ እንደነበርም ተመልክተናል።

ቁጥራቸው 7 የሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን እሳት አደጋ መከላከል ተሸከርካሪዎች ውኃ እና ኬሚካል በመርጨት የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች አንዳይዛመት ከፍተኛ ጥረት በማድረጋቸው እሳቱ 9፡20 አካባቢ ማጥፋት መቻሉን ባደረባችን መሳይ ገ/መድህን ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.