የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት 35ተኛ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳ የአልሚ ምግብ ጉዳይ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ


በኮሮና ቫይረስ ስጋት እና በደህንነት ጉዳዮችን ሽፋን በማድረግ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ጠንካራ የሴራ ስራዎች ተጎንጉነውበት የነበረው 35ኛ የህብረቱ ጉባኤ የአልሚ ምግብ ጉዳይ የዘንድሮው መነጋጋሪያ አጀንዳ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግዋል፡፡

ስማቸውን በውል መጥቀስ ያልተፈለጉ ተዋንያን በኮሮና ቫይረስ ስጋት እና በደህንነት ጉዳዮችን ሽፋን ጉባኤው በአካል በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ከፍተኛ ሴራ ላይ ተጠምደው መቆየታቸውን እና ይሄም በጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸውን መቀልበስ ተችሎ ጉባኤው፣በአካል በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መወሰኑን ጠቅሰዋል፡፡


የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት 35ተኛ የመሪዎች ጉባኤውን በመጪው ሳምንት በከተማችን ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል::
የህብረቱ የዘንድሮ አጀንዳም የአልሚ ምግብ ጉዳይ እንደሚሆንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል::

ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም
አብዱልሰላም አንሳር

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.