በጋና የማዕድን ማውጫ ከሆነችው ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ ከፍተኛ ፍንዳታ ቢያንስ 17 ሰዎች ሞቱ

በደቡብ ምዕራብ ጋና ከምትገኘው የማዕድን ማውጫ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ ከፍተኛ ፍንዳታ ቢያንስ 17 ሰዎች ሞተዋል፡፡

ፖሊስ እንዳለው፤ በጋና የማዕድን ማውጫ በሆነችው በደቡብ ምዕራብ ጋና በምትገኘው ቦጎሶ ከተማ ፈንጂዎችን የጫነ ከባድ መኪናና የሞተር ብስክሌት በመጋጨታቸው ምክንያት ነው ቢያንስ 17 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው፡፡

የሀገሪቱ የአደጋ ቁጥጥር ማኔጅመንት ከፍተኛ ሀላፊ እንደገለፁት 500 ቤቶች የአደጋው ሰለባ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡

ቢያንስ 59 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ጥቂቶቹ ጉዳታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት፡፡

የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ተገልጧል፡፡

የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ክስተት ነው ያሉ ሲሆን መንግስት ተጎጂዎችን በሚቻለው መንገድ ሁሉ ይደግፋል ብለዋል፡፡

ኤ ኤፍ ፒ

ሔኖክ አስራት
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *