ትዊተር የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የማህብራዊ ሚዲያ አካውንት መዝጋቱን አረጋገጠ

ያስቀምጥኩትን ደንብ በመጣስ በኢትዮጵያ ግጭት ትኩረት ያደረገ መረጃ ሲለጥፉ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አካውንት ዘግቻሁ ያለው ትዊተር አብዛኞቹ ግን የአማፂውን ቡድን የትግራይን ሀይል የሚደግፉ ተጠቃሚዎች ናቸው የትዊተር አካውንታቸው የተዘጋው ብሏል፡፡

ምንም እንኳ ትዊተር ትክክለኛ ቁጥር ባይገልፅም፤ የትግራይን ሀይል ደግፈው ግጭቱ ላይ መረጃዎችን በመለጠፋቸው አካውንታቸው የተዘጋባቸው በመቶዎች ይቆጠራሉ ብሏል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያው ለ ቢቢሲ እንደገለፀው ይሄ እርምጃ የተወሰደው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ በትዊተር የሚደረጉ ውይይቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን በምናደርገው ጥረት በርካታ ተጠቃሚዎች የትዊተርን መመርያና ደንቦች በመጣሳቸው ነው ብለዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ የኢትዮጵያን መንግስት የሚታገለውን የትግራይ አማፂ ቡድን የሚደግፉ የትዊተር ተጠቃሚዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተከታዮቻችንን እያጣን ነው፣ የምንከተላቸው ጓደኞቻችን ታገዱ እያሉ ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር፡፡

የትዊተር አካውንታቸው ከተዘጋባቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል አብዛኞቹ ለምን የትግራይን ሀይል የሚደግፉት የትዊተር ተጠቃሚዎች ሆኑ ለሚለው ጥያቄና ቅሬታ ምላሽ ሲሰጥ ትዊተር ፤ እኛ ደንብና መመርያውን ስናስፈፅም ካለ አድልዎ ነው ያለ ሲሆን ለፖለቲካ ማንነቶችና ርዕዮተ አለሞች አድልዎ እንዳናደርግ የምከተለው መርህና ውስጠ ደንብ ያስገድደናል ብሏል፡፡

አካውንታቸው የተዘጋባቸው ሁላ ውሳኔው ላይ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ ብሏል ተቋሙ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.