በመዲናዋ የኤሌክትሪክ አውቶብስን ስራ ላይ ለማዋል ፋይናንስ የማፈላለግ ስራ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በውጭና በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ለኤልክትሪክ አውቶብሶች ግዥ የሚውል ፋይናንስ እያፈላለገ እንደሚገኝ ያስታወቀው ቢሮው አውቶብሶቹ ሌሊት ቻርጅ አድርገው ቀኑን በሙሉ ያለምንም የጊዜ ብክነት አገልግሎት እንደሚሰጡም ያለውን እምነት አስታውቋል፡፡

አውቶብሶቹ የሙከራ ትግበራ የሚደረግባቸው በሸገር እና አንበሳ አውቶብሶች መሆኑን እና አገልግሎት የሚሰጡበት ከሸጎሌ ዴፖ ቅርበት ያላቸው አራት ኮሪደሮች ልየታ መከናወኑንም ይፋ አድጓል፡፡

ከዴፖው ያላቸው ርቀት፣ ከBRT ኮሪደሮች ጋር ያላቸው ትስስር እና ገበያ አካባቢዎች መሆናቸው ለኮሪደሮች የሙከራ ትግበራ መመረጥ እንደመስፈርት ተቀምጧል፡፡

የመጀመሪያው ኮሪደር ከአዲሱ ገበያ – ቄራ፣ ሁለተኛው ኮሪደር መነሻውን ዊንጌት አድርጎ መዳረሻው አየር ጤና፣ ሶስተኛው ኮሪደር ከለገሃር መዳረሻው ድል በር እንዲሁም አራተኛው ኮሪደር ከአውቶቡስ ተራ – አስኮ እንዲሆን መታቀዱንም ቢሮው አስታውቋል፡፡

በቀጣይ በከተማዋ ሌሎች ተጨማሪ ኮሪደሮችን በማጥናት የተደራሽነት አድማሱን የማስፋት ስራም እንደሚሰራ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *