በኬኒያ የመምህራን አገልግሎት ኮሚሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ናንሲ ማቻሪያ ሞቷል በማለት በፌስቡክ ገጹ የለቀቀውን መምህር፣ የሀገሪቱ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት (DCI) በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ኤርምያስ ምዋቩጋንጋ ሳሙኤል የተባለው ሰው የፌስቡክ ጽሁፍ ከመምህራን አገልግሎት ኮሚሽን ያገኘውት መረጃ ነው በሚል በውሸት የፌስቡክ አካውንት በከፈተው ገጹ ላይ ማጋራቱ ተሰምቷል፡፡
“ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኬንያ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት (DCI) ከጥናትና ምርምር መረጃ ቢሮ ጋር በትብብር መስራቱን በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል።
እንደ መርማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ፣ ለአራት ዓመታት በማኩኒ በሚገኘው የሙሲኒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ያገለገለው የ31 አመቱ ወጣት፣ የሃሰት መረጃውን ለማሰራጨት እንዲመቸው የሚያገለግል የስልክ ቀፎ ይዞ መገኘቱና፤የውሸት አካውንቱም የእሱ መሆኑ ተረጋግጧል።
ግለሰቡ በቅርቡ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የወንጀል ምርመራው ዳይሬክቶሬት ገልጿል።
መርማሪዎቹ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ያለአግባብ በመጠቀም ሌሎች ሰዎችን ለማሸበር ከሚያደርጉት ሴራ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
“ብዙዎች ይህንን የሚያደርጉት አንያዝም ብለው በማሰብ አሳሳች መልእክቶችን በመጻፍ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን የሚያውኩ በመሆኑ፣ እንደነዚህ አይነት ወንጀሎችን ለመከላከል አዲስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እያደረግን ነው” ብለዋል፡፡
ሃላፊው አክልውም ግለሰቡ የተያዙበትን መንገድ እንደምሳሌ ወስደው በዚህ ድርጊት ላይ የሚሳተፉ ሁሉ አጣርተን ለህግ እናቀርባልን ማለታቸውን ዴይሊ ኔሽን ነው የዘገበው፡፡
መሳይ ገ/መድህን
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም











