የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ‹‹በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ውይይት ለመቀጠል ‹ፖለቲካዊ ፍላጎት› ካለ በእኛ በኩል ዝግጁዎች ነን›› ብለዋል፡፡
ሹክሪ ይህን ያሉት በሙስካት ከኦማን አቻቸው ሰይድ ባድር አልቡሰይዲ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን የግብፅ መንግስት የዜና ወኪል ሜና ዘግቧል።
አልቡሳይዲ የግብፅን አቋም ‹‹ምክንያታዊ ነው ›› ያሉ ሲሆን ኦማንም ለዚህ ድርድር ያላትን ድጋፍ አረጋግጠዋል።
‹‹ ኦማን የሁሉንም ሀገራት ፍላጎት የሚያሟላ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ ተስፋ አድርጋለች›› ሲሉም ተናግረዋል።
ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም











