ከባሕር ዳር ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ለግዳጅ ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገው የሕዝብ ማመለሻ አውቶብስ በደረሰበት አደጋ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ታውቋል፡፡

የድሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ለአሚኮ በሰጡት ቃል ፥ ለግዳጅ ከባሕር ዳር የወጣው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ አደጋው እንደደረሰ ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው መለያ ቁጥሩ 11300፣ የጎን ቁጥሩ 2527 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋም 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የተናገሩት ኃላፊው ከእብናት ወደ አምደ ወርቅ ሲጓዝ ብዙ ሰው እንደነበርና ከአምደወርቅ ሲያልፉ ግን ሰው ያልነበረባቸው ወንበሮች እንደነበሩ ነግረውኛል ነው ያሉት፡፡

ለአደጋው ምክንያት ፍጥነት እና የመንገዱ መጎዳት ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አሚኮ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *