የቡርኪና ፋሶ መሪ በወታደሮቻቸው ታሰሩ

የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ክርስቲያን ካቦሬ በአማፂ ወታደሮች ታስረዋል፡፡

ሪዮተርስ ከሁለት የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ሰራተኞችና ከምዕራብ አፍሪካ ዲፕሎማት ያገኘሁት መረጃ ነው ብሎ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ በአማፂ ወታደሮች በጦር ሀይል ማዘዣ ካምፕ ታስረዋል

የቡርኪና ፋሶ መንግስት በትናንትናው ዕለት የወታደሮቹ እንቅስቃሴ መፈንቅለ መንግስት አለመሆኑን ገልጾ ነበር።

ሆኖም ግን የቡርኪና ፋሶ መንግስት ከትናንት ምሽት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የሰዓት ገደብ ጥሎ ነበር፡፡

በቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ውስጥ ጥያቄ እንዳነሱ የሚነገርላቸው አማጺ ወታደሮች አዛዦቻቸውን ጨምሮ መሪዎችን ገድለዋል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ ፕሬዝዳንቱ መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ሔኖክ አስራት
ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *