የብሔራዊ ሜትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የመጪውን የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ይፋ አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንዳሉት በመጪው የበልግ ወቅት በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የአየር ሙቀት ከመደበኛው አንጻራዊ መጨመር እደሚኖረው ትንበያው አመልክቷል፡፡
በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ፣ የሰሜን ምስራቅ ፣የመካከለኛውና የምስራቅ እንዲሁም የደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢች ደግሞ በአመዛኙ መደበኛ የሆነ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ በትንበያው ተመልክቷል፡፡
የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡- የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም











