በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን እግዱ ተነስቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከቀን 07/12/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሬት ነክ አገልግሎትን አግዶ መቆየቱ ይታወቃል።

ጊዜያዊ እግዱ አሁን የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከቀን 13/05/2014 ዓ.ም ጀምሮ በየክ/ከተማው ማግኘት ይቻላል።

ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር ከዚህ በታች የተገለጹት ናቸው ፦

 1. ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ
 2. የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት
  • የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት
 3. የስመ ንብረት ዝውውር ስራ
  • በባንክ ሐራጅ የተሸጠ
  • በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ
  • የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት
  • በውርስ የተላለፈ ንብረት
  • በReal estates አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ
 4. ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን
 5. የንብረት ግመታ
 6. በይዞታ ይገባኛል ክርክር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት
 7. የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/
 8. በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት
  • ካሣ ክፍያ
  • ምትክ ቤት
  • ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች
 9. የቦታ ዝግጅት
 10. የወሰን ማስከበር ተግባራት
 11. በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል
 12. የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ
 13. አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
  • የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው
  • ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣
  • የReal estates ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *