የማላዊ ፕሬዝዳንት የሚኒስተሮች ምክር ቤት አባላትን በተኑ፡፡

የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክወራ የካቢኔ አበላትን ከስራ ማሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይሕንን ውሳኔ ለማሳለፍ የተገደዱት አባላቱ የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡

በማላዊ በፈረንጆቹ 2020 ላይ በነበረው ምርጫ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ፕሬዚደንቱ፤ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ በሀገሪቱ ሙስናን ለመዋጋት አበክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዉ ነበር፡፡

ነገር ግን ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የገቡትን ቃል በአግባቡ አልፈጸሙም በሚል ቃላቸውን እንዲያከብሩ ከህዝባቸዉ የተለያዩ ግፊቶች ሲደረጉባቸዉ ቆይቷል፡፡

በዚህም ፕሬዚዳንቱ ሁሉንም የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ከስራ እንዲሰናበቱ ማድረጋቸውን ነው የተገለጸዉ፡፡

ይህንን ከባድ ውሳኔ ያሳለፍነው በሀገራችን ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ሲባል ነው የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በቀጣዮቹ 2 ቀናት ውስጥ ሌሎች የካቢኔ አባላትን በመመልመል አዲስ የሚኒስርቶች ምክር ቤት ይመሰረታል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ 3ቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ማለትም፤ የመሬት ሚኒስቴር፤ የሰራተኞች ሚኒስቴርና የኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መያዙም ተገለጿል፡፡

ምንጭ:-ቢቢሲ አፍሪካ

በጅብሪል መሃመድ
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *