የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሪፖርት ተቃውሞ ገጠመው፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የ2013 በጀት አመትን ” ግብ አምስት ” የስርአተ ጾታ እኩልነት ማረጋገጥ እና ሴቶችን ወደ ስልጣን ማምጣት ዝግጅት እና አፈጻጸም በተመለከተ ባቀረበው የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የክዋኔ ሪፖርቱን ያዳመጠው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳችዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት ላይ ቅር መሰኘቱን ገልጿል፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተቃውሞ የተነሱበት በ13 ጉዳዮች ላይ አጥጋቢ ምላሽ አልሰጠባቸውም ባላቸው ዝርዝር የክንውን ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ በሴቶች ላይ የሚቃጡ መድሎዎችን ለመለየት እንደዚሁም መድሎዎችን ለማስወገድ እና አፈጻጸሙን ለመከታተል የሚያስችል ስርአት በምላሹ ላይ አለመካተቱ አንደኛው ጉዳይ ነበር፡፡

የስርአተ ጾታ የመረጃ አያያዝ በተመለከተ የሚኒስትር መ/ቤቱ የመረጃ ቋት የቴክኖሎጂ እገዛ አነስተኛ መሆኑ እና የስርአተ ጾታ መረጃዎች ትክክለኛነት አጠራጣሪ መሆናቸው ቋሚ ኮሜቲው አስታውቋል፡፡

እንደዚሁም መስሪያ ቤቱ በክንውን ኦዲት ሪፖርቱ ሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች በሴተኛ አዳሪነት የሚደርስባቸውን ብዝበዛ የሚያሳይ መረጃ አላሳየም በሚልም ተቃውሞ ተነስቶበታል፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሴቶች ጉዳይ የሚሰሩ ስራዎች በየጊዜው የመገምገም የመከታተልና የመቆጣጠር ስራው የላላ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ የኦዲት ሪፖርቱ ላይ እነዚህንና ሌሎችም ጉለቶች አስተካክሎ እንዲገኝ ቋሚ ኮሚቴው ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡

ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *