የኬንያ ቁልፍ የመሠረተ ልማት ዕቅዶች በኢትዮጵያ ሰላም ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል የኬኒያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዩጵያ ያለውን ግጭት በመፍታት በመልሶ በመገንባት ላይ እንዲያተኩሩ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል ።

በናይሮቢ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኬንያታ የኬንያ ቁልፍ የመሠረተ ልማት ዕቅዶች በኢትዮጵያ ሰላም ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለውም ከናይሮቢ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የቴሌኮም ኢንቪስትመንት እንደ አንድ ቁልፍ ምሳሌ በመጥቀስ ይህ ዕቅድ በተረጋጋች ኢትዮጵያ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከቤተ መንግስት በላኩት መልእክት ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው ግጭት እነዚያን ዕቅዱች ሊጎትት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

“ጠንካራ ኢትዮጵያ ለኛ ጠቃሚ ነች። የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለእኛ ጠቃሚ ነች። ለዚህም ነው ግጭቱ እንዲፈታ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የያዝነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ኬንያታ ጎብኝት እያደረጎ ከነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ጋር ባደረጉት ውይይት አሳውቀዋል።

ከታቀደው ጊዜ ቀድመው ጉብኝታቸውን የጀመሩት ልዩ መልዕክተኛው ሳተርፊልድ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ለተከሰቱት ሁለት ቀውሶች መፍትሄ ለመፈለግ በቀጠናው እየተዘዋወሩ ይገኛሉ ሲል ኢስት አፍሪቃ ዘግቧል።

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.