ተቋርጠው የሰነበቱ የንብረት ሽያጭ፤ ስጦትን የማስተላለፍና ሌሎችም አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ሊመለሱ ነው፡፡

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑ ከሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጡትን አገልግሎቶች መስጠት የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ ቀደም በተለመደው አግባብ በተቋሙ አሰራር መሠረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት እና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የኦንላይን አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በተቋሙ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን አገልግሎቱ ገልፃል፡፡

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.