የተባበሩት አረብ ኤምሬት ኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የጉዞ እገዳ ልታነሳ ነው

አቋርጣው የነበረው የጉዞ እገዳ ዱባይ የፊታችን ቅዳሜ ልታነሳ ነው ተብሏል፡፡

በቅርቡ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ትራንዚትን ጨምሮ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ የከለከለቻቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካን፣ ኬንያን፣ ናይጄርያን እና ሌሎች ስምንት የአፍሪካ ሀገራትን ተጓዦችን ነበር፡፡

ሀገሪቷ ባለፉት አስራ አራት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 የአፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው የነበሩ ተጓዦች ወደ ሀገሬ መግባት አይችሉም ብላ እገዳ የጣለችው በልውጡ የኮቪድ 19 ህዋስ ኦሚክሮን ምክንያት ነው፡፡

ሌሎች እግዱ የሚነሳላቸው ሀገራት ታንዛንያ፣ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ቦትስዋና፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው፡፡

ማንኛውም ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬት ጉዞ የሚያደርግ ሰው ከመሳፈሩ ከ 48 ሰአታት በፊት ቀደም ብሎ ከኮቪድ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለበት፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሲደርስም ነፃ መሆኑን ተመርምሮ ማረጋገጥ አለበት፡፡

ሮይተርስ

ሔኖክ አስራት
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *