የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በጦርነቱ ለወደሙት በአማራ ክልል ከተሞች ከተሸከርካሪዎች ጀምሮ ከተሞቹ የከተማ አገልግሎት ስራዎቻቸውን ሊያስጀምሩ እንደሚገባ አስታወቁ

ሚንስትሯ ይህን ያሉት በደብረ ብርሃን ከተማ በክልሉ በጦርነቱ የወደሙ ከተሞችን በተዘጋጀውን የምክክር መድረክ ላይ ነው።

ከተሞቹን ስራ ለማስጀመር የሚያስችሏቸውን ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ለየከተሞቹ አመራሮች በማስረከብ ከተሞቹ ከነበሩበት በተሻለ እንደሚገነቡ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልፀዋል

በወራሪው ቡድን የወደሙ ከተሞችን ለማቋቋምና በተሻለ ደረጃ መልሶ ለመገንባት የከተማ አመራሮች በቁርጠኝት መስራት ይኖርብናል ሲሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ገልፀዋል፡፡

ሰላማዊ ከተሞች በጦርነቱ የወደሙ ከተሞች የደረሰባቸውን የመሰረተ ልማት ውድመት ብቻ ሳይሆን የከተሞቹ ነዋሪዎች ላይ የደረሱ ከፍተኛ የስነልቦና ስብራቶችንም በመጋራት አጋርነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል›› ያሉት ሚኒስትሯ ለከተሞች ከከተሞች በላይ ደራሽ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የከተሞች እህትማማችነት አጋርነት ጥምረት በሚል ሚኒስቴሩ ያስጀመረውን ከተሞችን የማስተሳሰር ተግባርም አጠናክሮ እየሰራበት ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.