የኩላሊት ህመምተኞች ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ከሁለት አመት በፊት በኮቪድ ምክንያት የተቋረጠው የኩላሊት ንቅለ ተከላ አሁንም አልተጀመረም፡፡

ይህንንም ተከትሎ በኩላሊት ህመም እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎች የድረሱልን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ከጅምሩ 42 ዜጎች ነበሩ ሆኖም ዛሬ ላይ ሁሉም በኩላሊት በሽታ ህይወታቸው አልፋል፡፡

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ለኩላሊት ህመምተኞች ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፏል።

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ አቅሙ የፈቀደው ሁሉ ከ2 ብር ጀምሮ በመርዳት ድምጽ አልባው በሽታ እንዋጋ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከ ጥር 26/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሚደረገው የ2 ብር ዘመቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢረባረብ ወገኖቻችንን ከሞት መታደግ እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ ሲመሠረት መስራቾቹ 42 ሰዎች የነበሩ ቢሆንም በአሁን ሰአት ሁሉም መስራቾቹ በህይወት የሉም ይህ ደግሞ በሽታው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያልና በመሆኑም ሁላችንም ወደየቤታችን እየመጣ ያለውን በሽታ በጋራ እንከላከል ብለዋል፡፡

በህመም እየተሰቃዩ ያሉ ዜጎች የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ቢሮ ድረስ እየመጡ የአንድ ቀን እድሜ እየለመኑን እንደሚገኙም ነው የተነገረው፡፡

በአሁን ሰዓት ለኩላሊት ህክምና ወጪ ለመሸፈን በየመንገዱ የምናያቸው የመኪና ላይ ልመናዎች አሰልቺ ሆኗል።

ለአንድ ኩላሊት ታማሚ ለህክምና ተብሎ ገንዘብ ሲሰባሰብ ለህክምና ሳይደርስ በኩላሊት እጥበት ብቻ የተሰበሰበው ገንዘብ ያልቃል ነው የተባለው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *