የዱባይ የሪል እስቴት ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊ እየሆነ መቷል፡፡

ዱባይ በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ወደ 36,000 መኖሪያ ቤቶችን ገንብታ ለማስረከብ እየሰራች መሆኑን khaleejtimes ዘግቧል፡፡

የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በሪል እስቴት ዘርፉ ላይ የሚከፈለውን የብድር-ወለድ መጠንን ዝቅ ማድረግ እና አዳዲስ የንግድ ተቋማትን መደገፍ የሪል እስቴት ገበያው እንዲያንሰራራና የኢንቨስትመንት ፍላጎቱም እንዲጨምር ረድቶታል ተብሏል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መንግስት አዳዲስ ፖሊሲዎቹን በመከለስ ሃገሪቱን ለቱሪስቶች መስህብ፤ ለንግድ ድርጅቶች እና ለነዋሪዎች የበለጠ ምቹና ተመራጭ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ዘገባው አክሏል ፡፡

በዱባይ የሪል እስቴት ቤቶች የሽያጭ እና የኪራይ ዋጋ በእጅጉ እየቀነሰ በመምጣቱ በዚህ አመት የቤት ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ታስቧል ተብሏል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በ2021 5,900 ቪላዎችን ጨምሮ 37,000 የመኖሪያ ቤቶች ለባለቤቶች ተላልፈዋል፡፡

በዚህ አመት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የርክክብ ስራዎችም የሚጠበቁ ሲሆን በ2022 ወደ 36,000 የሚሆኑ ቤቶች ለገበያ ለማቀረብ መታሰቡን ዱባይ እቅድ አላት ሲል khaleejtimes ዘግቧል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.