በኬንያ በሚኖሩ ምእራባዊያን ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈጽባቸው እንደሚችል ፈረንሳይ አስጠነቀቀች፡፡

በኬንያ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ በሀገሪቱ የፈረንሳይን ጨምሮ በሌሎችም ምእራባዊያን ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን እንዲሁ የውጪ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ የሽብር ጥቃቶች ሊያደርሱ እንደሚችሉ ጠቋሚ ነገሮችን መገንዘብ ተችሏል ብሏል ኤምባሲው፡፡

በመሆኑም የፈረንሳይ ዜጎችና ሌሎችም የውጪ ሀገር ጎብኚዎች በመዲናዋ ናይሮቢን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ባሉ ሙዚየሞች ና ሆቴሎች ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ከፈረንሳይ በተጨማሪም የኔዘርላንድና የጀርመን ኤምባሲዎች ዜጎቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ከዚሁ የኤምባሲዎች ማስጠንቀቂያ በኋላ የኬንያ ፖሊስ፤ በሀገራችን ከደህንነት አኳያ በዚህ ደረጃ የሚያሰጋ ነገር የለም፤ ቢሆንም ግን ዜጎች ለደህነታቸው የሚያሰጋ አጋጣሚ ሲያዩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንዳለባቸው ሲል ምላሽ ሰተዋል።

ኬንያ የአልሸባብ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት እንደፈረንጆቹ በ2011 ወደ ሶማሊያ ወታደሮቿን ካዘመተች ወዲህ በኬንያ በዚሁ የሽብር ቡድን የሚደርሱ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

ጅብሪል መሐመድ
ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.