ከጋምቤላ ክልል በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 6 ያክል ህፃናት ታፍነው ተወሰዱ፡፡

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት በተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሳቸውንና በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 6 ያክል ህፃናትን አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ተናግዋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከደብብ ሱዳን የሚነሱት የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከአኝዋክ ዞን አምስት ህፃናትን አፍነው የወሰዱ ሲሆን ከኑዌር ዞን ደግሞ አንድ ህፃን አፍነው መውሰዳቸውን ነግረውናል፡፡

እነኚሁ ታጣቂዎች አሁንም ቢሆን በሁለቱ ዞኖች ላይ የሚፈፅሙት ግድያ መቀጠሉን የነገሩን አቶ ኦቶው ታጣቂዎቹ በአንድ ወር ውስጥም በአስራ አንድ ሰዎች ላይ ግድያ መፈፀማቸውን እንዲሁም አራት ሰዎችን ማቁሰላቸውን ከመቶ በላይ የቀንድ ከብቶችንም በሁለት ዙር መዝረፋቸውን ነግረውናል፡፡

ያለውን ሁኔታ ለፌደራል መንግሰቱም ሆነ በጁባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቀናል ያሉን አቶ ኦቶው ኦኮት ድርጊቱን ለማስቆም ከዚህ ቀደም ከደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች ጋር በስልክ ተነጋግናል፣ ነገር ግን በቀጣይ ከደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች ጋር ፊት ለፊት በመገናኛት በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የውልሰው ገዝሙ
ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *