የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጤና ተቋማት በዱቤ የወሰዱት ተሰብሳቢ ብር በወቅቱ ገቢ ባለማድረጋቸው መቸገሩን አስታወቀ

መድኃኒቶችና የህክምና ግብቶችን ለመንግስት ጤና ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርበው መንግስታዊው ተቋሙ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳለጥ የተሰብሳቢ የዱቤ ሽያጭ የህክምና ግብቶችን በወቅቱ እና በበቂ መጠን ለማቅረብ ችግር እየተፈጠረበት መሆኑን የአገልግሎቱ የፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ገለጸዋል፡፡

ከአምስት አመት ጀምሮ ለሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት በአጠቃላይ ወደ 1.3 ቢሊየን ብር የዱቤ ሽያጭ አለመሰብሰቡን የተገለጸ ሲሆን ከፍተኛው የዱቤ ተሰብሳቢ በአዲስ አበባ በሚገኙ ጤና ተቋማት የወሰዱት እንደሆነ ተነስቷል፡፡

በክልል ከሚገኙ ቅርንጫፎች ባህርዳር 124 ሚሊየን ፣ አዳማ 91 ሚሊየን፣ ሀዋሳ 90 ሚሊየን ፣ ደሴና ጅማ 50 ሚሊየን ተሰብሳቢ ብር ያለባቸው ቅርጫፎች ለአብነት ተጠቃሽ መሆናቸውን አቶ ዘውዱ ተናግረዋል፡፡

የአገልግሎት ተቋሙ የተቋቋመበት ዓላማ ፈዋሽነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግስት ጤና ተቋማት ማቅረብ ሲሆን የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳለጥ የተሰብሳቢ የዱቤ ሽያጭ እብጠት መኖሩ ማነቆ እንደሆነበት ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የህክምና ግብቶችን ቶሎ ቶሎ በማሰራጨት ብዙ ሽያጭ እንዲኖረን እንፈልጋለን ያሉት ሀላፊው ከመንግሥት ካዝና በጀት የሚበጀትላቸው ጤና ተቋማት ያለባቸውን ብድር በወቅቱ እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

ችግሮቹ ተቀርፎው አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ ሽያጮች በካሽ የሚከናወኑበትን ና የእንዳስፈላጊነቱ የዱቤ ሽያጭ ፓሊሲ መመሪያ ሰነድ እንደተቀረፀ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.