ፑቲን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶሀንን የጎብኝት ግብዣ መቀበላቸው ተሰማ ።

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቱርኩ አቻቸው ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሀንን ፣ቱርክን እንዲጎበኙ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በትላንት እለት አሳውቀዋል፡፡

የቱርኩ የዜና ወኪል አናዶሉ እንዳለው ስብሰባው የሚካሄደው በኮቪድ ወረሽኝ እና በወቅታዊው ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጎዳዩች ላይ ነው ሲል ፔስኮቭ በሞስኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ።

“ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህን ግብዣ በምስጋና ተቀብለዋል ፣ በእርግጠኝነት ይህ ግብዣ ለሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ይጠቀማል” ሲሉ ፔስኮቭ ተናግረዋል፡፡

ፔስኮቭ ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት በሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የሚመራውን የመንግስታት ኮሚሽን እና የከፍተኛ ደረጃ ትብብር ምክር ቤት ስብሰባዎችን በማካሄድ ላይ “የተወሰነ ክፍተት” እንደነበረ ገልፀዋል።

ኤርዶጋን እና ፑቲን በየጊዜው በስልክ ከመነጋገራቸውም በላይ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በርካታ የጋራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.