ማሊ ከፈረንሳይ ጋር የገባችበት የግንኙነት መሻከር ዋንኛው ምክንያት ማሊ የፈረንሳይ ብሄራዊ ጥቅም እንደማታከብር በማሰቧ መሆኑን አስታወቀች፡፡

ፈረንሳይ ማሊን ጥቅሜን አታከብርም ብላ በመጠርጠሯ መሆኑን የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር አብዱላይ ዲዮፕ ከሩስያ ጋር በፈጠሩት ጥብቅ ወዳጅነት ሳቢያ ፈረንሳይ ሆዷ እንደሻከረ አስታውሷል፡፡

ፈረንሳይ በሆዷ ይዛው የቆየችውንም ቅሬታ ማሊ ከሩሲያ የገዛቸውን ወታደራዊ የጦር መሳሪያ ተከትሎ በግልጽ መታየት ጀምሮም እንደነበር አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ ከሩስያ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ያለን ከመሆኑ ባሻገር ከሌሎች መፈንቅለመንግስት ካከናወኑ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ጥሩ ወዳጅነት የመሰረተችው ፈረንሳይ ማሊን አመት ባለፈው ወታደራዊ መፈንቅለመንግስት ህጋዊነት ላይ ጥያቄ ማስነሳቷ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

በማሊ በሺዎች የሚቆጠሩ የፈረንሳይ ወታደሮችም የሃገሪቱን ወታደሮች በማማከር እና በድጋፍ እያገለገሉ እንደሚገኙ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *