በኬንያ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በሰሜናዊ ኬንያ ማንድራ ከተማ ውስጥ የቦምብ ፍንዳታ መድረሱን ተከትሎ 10 ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ቢቢሲ አፍሪካ አሁን በሰበር መረጃው ዘግቦታል፡፡

ከተማዋ ኬንያ ከሶማሊያ የምትዋሰንበት ስትሆን ይህ ጥቃት በአል ሸባብ የተቀነባበረ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ተብሏል፡፡

ጥቃቱ የደረሰው በኬንያ የሚገኙ የአውሮፓ ሀገራት ኤምባሲዎች፤ በአሸባሪዎች ጥቃት ሊሰነዘር ይችላልና በሀገሪቱ የሚገኙ ምእራቢዊያን ዜጎች እንዲጠነቀቁ ማስጠንቀቂያ በሰጡ በቀናት ውስጥ የደረሰ ነው፡፡

የአልሸባብ የሽብር ቡድን በተለይም ኬንያ ቡድኑን ለመዋጋት እ.ኤ.አ. በ2011 ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ካዘመተች ጀምሮ፤ ከሶማሊያ በተጨማሪ ኬንያንም አንዱ የጥቃቱ ኢላማ በማድረግ በርካታ የሽብር ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛል፡፡

ጅብሪል መሐመድ
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.