በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረገ

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ እና ከመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የተውጣጣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

ቡድኑ ባለፉት አራት ቀናት በነበረው ቆይታ በሪያድ ከኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አመራሮች እና አባላት፣ ከሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የተወያየ ሲሆን፣ ከሳዑዲ መንግስት በኩል ከአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል አብዱል አዚዝ ቢን ሳዑድ ቢን ናየፍ፣ ከሳዉዲ ሮያል ፍርድ ቤት አማካሪ እና የንጉስ ሰልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል የበላይ ተቆጣጣሪ ከሆኑት ከዶ/ር ቢን አብዱልአዚዝ አል ራቢህ ጋር መወያየቱ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የልኡካን ቡድኑ ከእስላማዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር አልዱልላቲፍ አልዱልአዚዝ አል-ሼይክ፣ ከፋይናንስ ሚስትር ሞሃመድ ቢን አብዱላህ አልጀዳን እንዲሁም ከሳዉዲ የልማት ፈንድ የኦፕሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከኢንጂነር ፈይሰል መሀመድ አል-ቃህታኒ ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅትም እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አያያዝ ስለሚሻሻልባቸው፣ የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተቃጠለና የተለያዩ ቅጣቶች የሚጠብቋቸው ነገር ግን በራሳቸው ገንዘብ ተሳፍረው አገራቸው መግባት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቅጣት ተነስቶላቸውና ምህረት ተደርጎላቸው ወደ አገራቸው መመለስ በሚችሉባቸው አግባቦች መነሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.