ታሊባን ወደ 100 የሚቆጠሩ የቀድሞ የአፍጋኒስታን ባለስልጣናትን መግደሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ አመልክቷል፡፡

በነሀሴ ወር ታሊባን ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ከ100 በላይ የቀድሞ የአፍጋኒስታን መንግስት አባላት፣ የጸጥታ ሃይሎች እና ከአለም አቀፍ ወታደሮች ጋር ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቡች ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ አመልክቷል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደተናገሩት ከተጠቂዎቹ ውስጥ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት በታሊባን ወይም በተባባሪዎቹ ያለፍርድ ተገድለዋል ።

“ለቀድሞ የመንግስት አባላት፣ የጸጥታ ሃይሎች እና ከአለም አቀፍ ወታደራዊ ሃይሎች ጋር አብረው ለሰሩት አጠቃላይ የምህረት አዋጁ ቢታወጅም የግድያ መሰወር እና ሌሎች ጥሰቶችን የተመለከተ ተአማኒነት ያለው መረጃ እየደረሱት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሰረት 22.8 ሚሊዮን ሰዎች በከፋ ችግር እና በምግብ ዋስትና እጦት ውስጥ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ግማሾቹ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *