የአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳት ስራ ተጠናቀቀ፡፡

በ1927 ዓ.ም ሀገርን ከጠላት ወረራ ለመታደግ ይቻል ዘንድ ሀገር ፍቅር ማህበር ተብሎ የተመሰረተውና ቀጥሎ በ1960 ዓ.ም ሀገር ፍቅር ቴአትር ተብሎ የተቋቋመው አንጋፋው ቴአትር ቤት ታሪካዊ ይዘቱንና የምህንድስና ጥበቡን ሳይለቅ ዘመኑን እና የቴአትር ቤቱን ስም በሚመጥን መልኩ ዕድሳቱ ተጠናቆ የመጀመሪያ ርክክብ መደረጎ ተነግሯል፡፡

ላለፉት 20 ዓመታት ዕድሳት ተደርጎለት እንደማያውቅ የተነገረው ቴአትር ቤቱ የዕድሳት ስራው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተከናውኖ በዛሬው ዕለት ርክክብ መደረጉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

610 መቀመጫዎች አሉት የተባለውን ዋናውን የቴአትር ማሳያ አዳራሽ ጨምሮ አርት ጋለሪ፣አነስተኛ የቴአትር አዳራሽ፣ ዘመናዊ የሙዚቃ መከወኛ ክፍል፣ ካፊቴሪያ፣ አስተዳደር ህንፃ እና ሌሎችም አገልግሎቶች የተካተቱበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቴአትር ቤቱ ለተደራሲው ከፍ ያለ ምቾትን ከማጎናፀፉም በተጨማሪ የጥበብ ሰዎችንም ለተሻለ የፈጠራ ስራ የሚያነሳሳ ምቹ እና ፅዱ የኪነጥበብ ቤት ሆኖ የዕድሳት ስራው ተጠናቋል ነው የተባለው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *