የአፍሪካ ህብረት ተገቢውን የአባልነት መዋጮን ያልከፈሉ 14 ሃገራት ላይ ከአባልነት እስከማገድ እርምጃን እንደሚወስድ አሳሰበ፡፡

ህብረቱ የሚተዳደርበትን የአባልነት መዋጮ ባለመክፈላቸው አምስት ሃገራት ከዚህ ቀደም ከአባልነት ማገዱ የሚታወስ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሊቢያ ሶማሊያ ቡሩንዲ እና ሲሸልስን የሚገኙበት ሲሆን በአምስተኛነትም ጎረቤት ሱዳን የእገዳው ሰለባ መሆኗም ይታወቃል፡፡

በ2021 የፈረንጆች አመት የሚጠበቅባቸውን የአባልነት መዋጮ ቢያንስ ግማሹን እንኳ ለህብረቱ ገቢ ባላደረጉ 14 አባል ሃገራት ላይ ህብረቱ ከአባልነት የማገድን ማስጠንቀቂያ አውጥቶባቸዋል፡፡

የእግዱን ጉዳይ አስገራሚ ያደረገውም የህብረቱ ቀጣይ ሊቀመንበር የምትሆነው ሴኔጋልም ክፍያውን አለማከናወኗ ነው፡፡

በዚህኛው ዝርዝር ውስጥ አንጎላ፣ ጊኒ እና ከአፍሪካ ባለ ቀደምት ኢኮኖሚዋ ናይጄሪያም በዚሁ የባለእዳ መዝገብ ላይ ሰፍረዋል፡፡

ይህ የአባላት መዋጮ በተገቢው ጊዜ አመሰብሰብ በህብረቱ ስራ አፈፃፀም ጥንካሬ እና የበጀት ምደባ ላይ ጥላ ማጥላቱም አይቀሬ ነው፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *