ግብጽ በ10 የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላት ላይ የሞት ፍርድ እንዲጸና ወሰነች

የግብጽ ፍርድ ቤት የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላት የሆኑ 10 ሰዎች፤ በሞት እንዲቀጡ መወሰኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ የሚዲያ ኤጀንሲ MENA ዘግቧል፡፡

በሞት እንዲቀጡ ምክንያት የሆነውም እነዚህ ግለሰቦች በሀገሪቱ የፖሊስ ተቋም ላይ አውዳሚ ጥቃት ለመፈጸም ሲያቅዱ ሲዘጋጁና ሲያሰሩ ተደርሶባቸዋል በሚል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

እስካሁን የግለሰቦቹ ማንነት በዝርዝር ያልተገለጸ ሲሆን፤ ዘጠኙ ከዚህ በፊት በፍርድ ሂደት ላይ እንደነበሩና የአንዱ ግለሰብ ግን ውሳኔው የተላለፈው በሌለበት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ውሳኔውም በሀገሪቱ ከፍተኛው የሀይማኖት ተቋም ካየው በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ በግብጽ መንግስት በሽብረተኝነት የተፈረጀ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ጅብሪል መሐመድ
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.