ነገ ለሚጀመረው የአፍሪካ ህብረት 40ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ የየሀገራቱ አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ስብሰባውን የሚታደሙ የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመራሮች አዲስ አበባ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
የሶማሊያው የውጭ ጉዳይዮችና አለም አቀፍ ትብብር ሃላፊው አብዲ ሴድ ሙሴ አሊ፤ የዚምባቡዌው የውጭ ጉዳዮች ሚኒስትር ሚስተር ፍሬድሪክ ሙሲዋ ማካሙሬ፤ እንዲሁም የሳኦቶሜና የሌሎችም የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች ፤ ስብሰባውን ለመካፈል ከተገኙት አመራሮች መካካል ናቸው ብሏል፡፡
ታዳሚዎቹ ቦሌ አለም አቀፈ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፈይሰል አሊ ትላንት ደማቅ አቀባባል አድርገወላቸዋል፡፡
40ኛው የህብረቱ መደበኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ነገና ከነገ ወዲያ ለ2 ቀናት እንደሚቆይ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል፡፡
ከዚሁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክክር በኋላ የፊታችን ቀዳሜነና እሁድ ደግሞ የሕበረቱ 35ተኛው መደበኛው የመሪዎች ስብስበ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን 25 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ስብሰባው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች በሙሉ በኢትዮጵያ በኩል መደረጋቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጅብሪል መሐመድ

ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *