ኢትዮ ቴሌኮም እስከ አራት ቢሊየን ወርሃዊ የካርድ ሽያጭ እንደሚያከናን ገለጸ

ኢትዮ ቴሌኮም ዋና የሽያጭ ሀላፊ አቶ መሀመድ ሀጂ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ኩባንያቸው በየወሩ አራት ቢሊየን ብር የካርድ ሽያጭ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ይሕንን ያህል የካርድ መጠን ከውጭ ይገዛ እንደነበር ያነሱት ሃላፊው ፣ የካርድ ህትመቱን ሀገር ውስጥ ማድረግ በመቻላችን ይህንን ገንዘብ በሽያጭ ማግኘት ችለናል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ለካርድ ህትመት ኢትዮ ቴሌኮም እያወጣ ያለው 20 ከመቶ ብቻ እንደሆነ የገለጸው ኩባንያው ነባሩን የሞባይል ካርድ ወደ ወረቀት ከቀየረ በኃላ 80 ከመቶ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ ማዳን መቻሉንም አቶ መሀመድ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ካርድ ሽያጭ የሚያደርገው በሶስት አይነት መንገድ እንደሆነ የተናገሩት ሀላፊው ከውጭ ታትሞ የሚመጣው ማለትም (የሚፋቀው ካርድ)፣ በኤሌክትሮኒክስ የሚደረገው ሽያጭ እና የወረቀቱ ይገኝበታል ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ የባለ 50 እና የባለ 100 ብር የወረቀት ካርድ መጥፋቱ ፣በወረቀት ካርዱ ላይ በተፈጠረ እጥረት ሳይሆን ካርድ ለማከፋፈል በገቡ አዳዲስ ወኪሎች ሂደቱን ጠንቅቀው ባለማወቃቸው እንደሆነ ተናግዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.