በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ በሰነድና በፎቶግራፍ የተደገፈ የተሽከርካሪዎች ቆጠራ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ቆጠራው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ያግዛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም ቆጠራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በቢሮው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሰፋ እንደገለፁት የተሽከርካሪዎች የአካል ቆጠራ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ስራ ላይ ያሉትን ተሽከርካሪዎች በማወቅ በአግባቡ ለማስተዳደር ይረዳል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር እስካን የነበረውን የተሽከርካሪ ቁጥር በማደስ ትክክለኛውን መረጃ ለማወቅም ጭምር ታሳቢ ተደርጎ የቆጠራ ስራው እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሁለት ኮድ 1 ታክሲ እና አንድ የሀይገር ባለንብረቶች ማህበራት በቅርንጫፉ መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ጀማል ከመደበኛ የስራ ቀናት እና ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጭ ባሉት ጊዜያት የቆጠራ ስራው እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከዚህ በፊት በተያዘው መረጃ ከ1 ሺህ በላይ ታክሲ ተሽከርካሪዎች እንዳሉ መረጃው እንደሚያሳይ የጠቆሙት አቶ ጀማል አሁን በስራ ላይ ያሉት ከ450 እንደማይበልጡም አስታውቀዋል፡፡

በዚህ የተነሳ ከተሽከርካሪ ቁጥር አንፃር ልዩነት መኖሩን ስራ አስኪያጁ ገልጸው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያሉ መረጃዎችን ጭምር ለማጥራት የቆጠራ ስራው በሰነድና በፎቶግራፍ በማስደገፍ በትኩረት እየተተገበረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *