በኮንጎ የሃይል ማስተላለፊያ ገመድ በመቆረጡ ከ25 የሚልቁ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡

በገበያ ቦታ እንደወደቀ የተነገረው የሃይል ማስተላለፊያ ገመዱ 26 ሰዎችን እንደገደለ የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በኪንሻሳ በሚገኙ ንግድቤቶች ላይ የወደቀው ከፍተኛ ሃይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ገመዱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን በማህበራዊ ትስስር ገጾችም የሚዘዋወሩ ምስሎች አሳይተዋል፡፡

ምን እንደቆረጠው ያልታወቀው ይህ የኤሌክትሪክ ገመድ በአካባቢው ዘንቦ ስለነበር ከጎርፉ ጋር ተዳምሮ ጉዳቱን ከፍ እንዲል አድርጎታልም ተብሏል፡፡

በአደጋው ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በአካባቢው የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሴቶች መሆናቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ቢቢሲ

አብድልሰላም አንሳር
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *