የአሜሪካ መንግሰት ኤጀንሲ፤ በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከሚያደርጋቸው የገንዘብ ድጋፎች መካካል ለቡርኪናፋሶ የሚሰጠውን 450 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማቋረጧን አስታውቋል፡፡
ድጋፉን ለማቋረጡ ምክንያት የሆነውም ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ ናቸው የሚባልላቸው የቀድሞ የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬን፤ በወታደራዊ ሃይሉ በመፈንቅለ መንግስት መነሳታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡
የገንዘብ ድጋፉን የሚያደርገው በአሜሪካ በምህጻሩ MCC ተብሎ የሚጠራው ገለልተኛ ተቋም ሲሆን ዋና አላማውም፤ በሀገሪቱ መልካም አስተዳደርን ለመገንባት የሚውል ነው ብሏል፡፡
ቢሆንም ግን አመጽና መፈንቅለ መንግስት እንዲነሳ በማድረግ ገንዘቡ ከተመደበለት አላማ ውጪ በመዋሉ ድጋፉ እንዲቆም ተደርጓል ብሏል ተቋሙ፡፡
ያሳለፍነው ሳምንት በቡርኪናፋሶ የመንግስት ግልበጣ በማድረግ አዲስ ወታደራዊ መንግስት መመስረቱ ይታወሳል፡፡
ኤ.ኤፍ.ፒ
ጅብሪል መሃመድ
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም











