እየተካሄደ ካለው የአፍካ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን የየሃገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ እየመከሩ እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡
የበርካታ ዲፐሎማሲያዊ ተቋማት እና የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ 40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከጉባኤው ጎን ለጎን የሊቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአልጄሪያ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከአንጎላ አቻዎቻቸው ጋር መምከራቸውን ፓናማ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ዛሬ የተጀመረውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ያስጀመሩት ሲሆን “በአፍሪካ በየአቅጣጫው እያጋጠመ ያለውን የተለያዬ ቅርፅ የያዘውን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው ጥረት፣የአጀንዳ 2063 የአፈጻጸም ሂደት ፣የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አተገባበር እንቅስቃሴ እና መሰል ወቅታዊ የአህጉሪቷን አጀንዳዎች ማንሳታቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መግለጫ ያሳያል፡፡
አብድልሰላም አንሳር
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም











