“የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል 40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በስብሰባው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የአስፈጻሚ ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሄደው 35ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአስፈጻሚ ምክር ቤት በኅብረቱ አባል አገራት የጋራ ፍላጎት የሆኑ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም











