5ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድን አስመልክቶ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም፡-
• ከአዋሬ በጥይት ቤት ወደ ፓርላማ
• እንዲሁም ከቡልጋሪያ ወደ አፍሪካ ኅብረት የሚወስዱ መንገዶች በሁለቱም አቅጣጫ የስብሰባው ተካፋዮች ጠዋት ለስብሰባ፣ ለምሳና ከሰዓት በኋላ ከስብሰባ ሲወጡ እነዚህ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት ለአጀብ ሥራ መንገድ ሲዘጋ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች ትዕግስት ተላብሰው በመጠበቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያርጉ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪውን እያቀረበ ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
• ከፓርላማ መብራት – በውጭ ጉዳይ ሚ/ር – መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ – ኦምሎፒያ – ወሎ ሰፈር – ጃፓን ኤምባሲ – ፍሬንድ ሺፕ – ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – በብሄራዊ ቤተ – መንግስት – በፍልውሃ – በብሄራዊ ቲያትር – ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ፡-
• ከፓርላማ መብራት – ብሔራዊ ቤተ-መንግስት – ወዳጅነት ፓርክ – ንግድ ማተሚያ ቤት – ሞናርክ ሆቴል – ቴዎድሮስ አደባባይ – ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል – ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን – ብሔራዊ ቴአትር – ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት
• ከፓርላማ መብራት – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን – ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን
• ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ – አፍሪካ ህብረት ዋናው በር – ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዓርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ሲሆን
• ከጦር ሃይሎች – ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ፦
• በኮካ-ኮላ ድልድይ – በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር – ጎማ ቁጠባ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፡- ሳር ቤት – ካርል አደባባይ – በልደታ አድርገው ወደ መርካቶ እና ጎማ ቁጠባ
• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፦
• በአትላስ – ዘሪሁን ህንፃ – ሲግናል
• ቀለበት መንገድ – ቦሌ ሚካኤል – ሃኪም ማሞ – ወደ ጎተራ
• ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ – እንግሊዝ ኤምባሲ
• ቀለበት መንገድ – መገናኛ – አድዋ ጎዳና – አዋሬ – ቤልኤር
• በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥመው ጥቆማ ለመስጠት በመደበኛ ስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም 987፣ 991 እና 916 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችል ግብረ-ኃይሉ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.