በተለያዩ መመዘኛዎች የአለም ከተሞችን ያወዳደረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩስያዋን ዋና ከተማ ሞስኮን ለኑሮ አመቺ ከተማ ሲል ሰይሟታል፡፡
መዲናይቱ ከአውሮፓ እና ከሰሜን አሜሪካ ከተሞች ጋር የተነፃፀረች ሲሆን በ2022 የቀዳሚነት ደረጃን መጎናፀፏን ተመድ አስታውቋል፡፡
በተለያዩ መስኮች የተደረገው ጥናቱ 50 ከተሞች የተነፃፀሩበት ሲሆን መመዘኛውም የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የኑሮ ደረጃ፣ ማህበራዊ መስተጋብር፣ የከባቢ አየር ጤናማነት ደረጃ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር እና የህግ ድንጋጌዎች በዋናነት ከግንዛቤ መግባታቸውም ተሰምቷል፡፡
ሞስኮን ቀዳሚ ያደረገው ረቂቅ ሰነዱ ሲንጋፖር እና ቶሮንቶን በቅደም ተከተልነት ሲያስቀምጥ ሲድኒን እና ለንደንን በአራት እና በአምስተኛነት ደረጃ ማስፈሩን የዘገበው አርቲ የዜና ወኪል ነው፡፡
አብዱሰላም አንሳር
ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም











