የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ተቃዋሚ ሃይሎች ከግብጽ ጋር የሚያገናኘውን አውራ ጎዳና ከዘጉ ዘጠኝ ቀናት ሞላቸው

በሱዳን ከሶስት ወራት በፊት በሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ዋነኛ ክንፍ የነበረው የጦር ሃይሉ፤ ባደረገው የመንግስት ግልበጣ የሲቪሉን አስተዳዳር መናዱ የሚታስ ነው፡፡

ምንም እንኳን የሐገሪቱ ጦር በመፈንቅለ መንግስት ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ቢመሰርትም፤ በአብዛኛው የሐገሪቱ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ያላባራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

አሁንም ቢሆን ወታዳራዊ አገዛዙ ይቁም የሲቪሉ አስተዳዳር ወደ ቦታው ይመለስ ሲሉ ህዝቡ ለተቃውሞ እየተመመ ይገኛል፡፡

ከሱዳን ህዝቦች መካከል በአብዛኛው ገበሬዎች ናቸው የተባሉ የወታደራዊ መንግስቱ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ሱዳንን ከግብጽ ጋር የሚያገናኘውን ዋና ጎዳና ከዘጉ ከሳምንት በላይ ሆኗቸዋል፡፡

መንገዱን በድንጋይ እና በእንጨት መዝጋታቸውን ተከትሎ ከግብፅ የሚመጣም ሆነ ከሱዳን ወደ ግብጽ የሚሄድ ማንኛውም ተሽከርካሪ እንዳያልፍ በተጠንቀቅ እየጠበቁ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የእንስሳት እና የሌሎችም ሸቀጣሸቀጦች የንግድ ለውውጥ መስተጓጎል እንደገጠመው ታውቋል፡፡

ከዚህ ባላፈ ደግሞ ተቀዋሚዎቹ ከሱደን ወደ ግብጽ በገፍ የሚላኩ እንስሳትን እና የግብርና ምርቶችን እንደማይፈልጉም መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በአሁኑ ሰዓት እንስሳትን ጨምሮ በርካታ ሸቀጣሸቀጦችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በበረሃማው ጎዳና ላይ ረዥም መስመር ሰርተው ቆመው እንደሚገኙ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል ያሳያል እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ፡፡

ጅብሪል መሃመድ
ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.