ከመነጨው ኤሌክትሪክ ውስጥ 7 ሺህ 372 ጊጋ ዋት ሰዓት ከውሃ፣ 270 ነጥብ 59 ጊጋ ዋት ሰዓት ከንፋስ እና ቀሪው 24 ነጥብ 8 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ደግሞ ከእንፋሎት የመነጨ ነው፡፡
ተቋሙ በ6 ወራት ውስጥ ለማመንጨት ያቀደው ወደ 9 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ቢሆንም 7 ሺህ 668 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ በማመንጨት የዕቅዱን 84 ነጥብ 4 በመቶ አሳክቷል፡፡
በግማሽ ዓመቱ የመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ያደረሰው ውድመት ለዕቅድ አፈፃፀም ልዩነቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ተቋሙ በጦርነቱ ሳቢያ የተከዜና የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ ካለመቻሉም ሌላ ተቋሙ ያቀደውን የኢነርጂ ምርት ለማሳካት ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም











