የጤና ሳይንስ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች የኩላሊት እጥበት ሊጀመር ነው፡፡

ከጤና ሚኒስትር ጋር መተባበር በክልል ከተሞች የኩላሊት እጥበት ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ፡፡

በኢትዮጵያ የኩላሊት ታካሚዎች ቁጥር በየአመቱ መጨመሩን ተከትሎ የኩላሊት እጥበት በመላው የሀገሪቱ ክፍል ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

አቶ ሰለሞን እንዳሉት የጤና ሳይንስ ትምህርት በሚሰጥባቸው 13 ቦታዎች ላይ የኩላሊት እጥበት ይጀመራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከገንዘብ እጥረት ጋር በተያያዘ 2ሺህ የሚጠጉ የኩላሊት ታካሚዎች የመንግስት ሆስፒታል ለመግባት ወረፋ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በመንግስት ሆስፒታል ለድሀ ድሀ ታካሚዎች ህክምናው በነጻ እየተሰጠ ሲሆን በግል ሆስፒታሎች በሳምንት ለኩላሊት እጥበት እስከ 8ሺህ ብር እንደሚደርስ ነው የተገለጸው፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከተቋረጠ ሁለት አመታት ያለፈው መሆኑን ያለሱት ስራአስኪያጁ፣ ከሰሞኑ ንቅለ ተከላው ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ከ400ሺህ በላይ ዜጎች መኖራቸው ይነገራል፡፡

በሚኒሊክ ሆስፒታል ተቋጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ከሰሞኑ በ30 ያህል ማሽኖች ይጀመራል ተብሏል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *