በበሻሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን ተከሰተ?

በዛሬው እለት በበሻሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቀኑ 6 ሰአት አካባቢ አንዲት ተማሪ ከአራተኛ ፎቅ ላይ እራሷን ጥላለች፡፡

እራሷን ከፎቅ ላይ የጣለችው ተማሪ ወዲያወኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰደች ሲሆን በጊዜው ሂይወቷ አለማለፉን ተመልክተናል፡፡

የተማሪዋ መውደቅ ተከትሎ በስፍራው የነበሩ በርካታ ተማሪዎች እራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

የአስረኛ ክፍል ተማሪ እንደሆነች የተነገረው ተማሪዋ ከቤተሰቦቿ ተጣልታ ወደ ትምህርት ቤት መምጣቷን ነው የተነገረው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የትምህርት ቤቱን መምህራን አግኝቶ ስለተፈጠረው ክስተት የጠየቀ ሲሆን ተማሪዋ እንደተባለው ከቤተሰብ ጋር ተጣልታ ነው ለዚህ ውሳኔ የደረሰችው ብለውናል፡፡

ቁጥራቸው ከ100 በላይ የሚደርሱ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በተለይም የልብ ድካም እና ድንጋጤ የተሰማቸው ተማሪዎች አቅራቢያ ወደ ሚገኙ ሆስፒታሎች እየተወሰዱ ኢትዮ ኤፍ ኤም በስፍራው ሆኖ ተመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትም በትምህርት ቤቱ የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራት ቦታው ደርሰው ጉዳዩን እያጣሩ ነበር፡፡

በጉዳዩ ዙርያ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሙሉ መረጃውን አጣርቶ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *